የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

By Tibebu Kebede

April 07, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ ተገለፀ።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት አንቀጽ 57 ንጹስ አንቀጽ 3/1 እና የይቅርታ ደንብ 114/98 በሚያዘው መሰረት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለ13 ሺህ 231 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲለቀቁ ወስነዋል።