Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌና አካባቢው በ31 ቅርንጫፎች ዳግም ሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል በመቀሌ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታወቀ፡፡
 
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ንግድ ባንክ በመቀሌና አካባቢው በ31 ቅርንጫፎች ዳግም የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ዛሬ ከሰዓትም 16 የሚሆኑ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ነው የባንኩፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የገለጹት፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ውሳኔን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ 5 ቢሊየን ብር ጥሬ ገንዘብ ወደ መቀሌ መላክ መጀመሩ ይታወቃል።
ይህ ጥሬ ገንዘብ ከትናንት ጀምሮም ለባንኮች መሠራጨት እንደሚጀምር ነው በወቅቱ የተገለፀው።
በደስታ ተካ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.