Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የፍልሰት ጥናትና ምርምር ጉባዔ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የፍልሰት ጥናት እና ምርምር ጉባዔ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ የፍትሕ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ አለምአንተ አግደውን ጨምሮ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኙ የተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ከጉባዔው አዘጋጅ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ አጥኚዎች እና ተመራማሪዎችም በመድረኩ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉባዔው ዓላማ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ከመከላከል አንጻር በጥናት በተለዩ ተጨባጭ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ ጥናታዊ ግኝቶቹ በቀጣይ ስለሚተገበሩበት ሁኔታ ለመምከር ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ ሰባት የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.