የሀገር ውስጥ ዜና

አራት የስኳር ፋብሪካዎች ከ506 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ማምረታቸው ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

February 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት የስኳር ፋብሪካዎች እስከ ትናንት ድረስ 506 ሺህ 121 ኩንታል ስኳር ማምረታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡

ምርቱ ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ መሆኑን በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ስኳሩን ከሕዳር መጨረሻ ጀምሮ ያመረቱት ፋብሪካዎችም ወንጂ፣ ፊንጫ፣ ኩራዝ 2 እና ኩራዝ 3 መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ማምረት ይጀምራል ነው ያሉት።

እንዲሁም ጣና በለስ፣ ከሰም እና አርጆ ዴዴሳ የስኳር ፋብሪካዎች በቀጣይ ወደ ምርት እንደሚገቡ አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!