የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ማክሮን ጋር በፓሪስ መከሩ

By ዮሐንስ ደርበው

February 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ መከሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ ጉብኝታቸው ከጣሊያን እና ማልታ በመቀጠል ፈረንሳይ፣ ፓሪስ ገብተዋል።

በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መግለጫም “ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን በማግኘቴ ደስ ብሎኛል” ብለዋል።

“በፓሪስ ስለተደረገልን አቀባበል እናመሰግናለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየጠነከረ ሲሄድ፥ ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንደሚሸጋገር እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት እንደሚያበረታቱም አስታውቀዋል።