የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

February 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ 6 ወራት ዕቅድ ግምገማ እየተካሄደ ነው።

በግምገማው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት እና የተቋማት የስራ ሀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡላንግ ጋች እንዳሉት የክልሉ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ወደ ትግበራ ከገባ ሶስት ዓመታትን አስቆጥሯል።

አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችም የ10 ዓመቱን መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ያደረገ የ2015 ዓመታዊ ዕቅድ አዘጋጅተው ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡