የሀገር ውስጥ ዜና

በግብርናው ዘርፍ የማደርገውን ድጋፍ እቀጥላለሁ- ፋኦ

By ዮሐንስ ደርበው

February 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ከዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሞድዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

አቶ ግርማ በውይይቱ ላይ ድርጅቱ የግብርናውን ዘርፍ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀው÷ ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮችንም አብራርተዋል፡፡

ፋራይ ዚሞድዚ ድርጅቱ የግብርናውን ዘርፍ ለመደገፍ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር የሚያከናውናቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ፣ በሰብል እና የእንስሳት ልማት ላይ ከሚኒስቴሩ ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ መግለጻቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!