የሀገር ውስጥ ዜና

በከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች የሶስት ወር ቅድሚያ ክፍያ እንዲከፈላቸው ተወሰነ

By Tibebu Kebede

April 08, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል የከተሞቸ ልማታዊ ሴፍቲ ኔት ፕሮጀክት ስቲሪንግ ኮሚቴ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር በተያያዘ በዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

ኮሚቴው ባካሄደው ስብሰባ ከከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ተጠቀሚዎችና ተጋላጭ የሆኑ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የሚያጋጥማቸውን ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች አፋጣኝ የሚፈቱበትን ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ውሳኔ አሳልፏል።