የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የዕሳት አደጋ የእናት እና ልጅን ህይወት ቀጠፈ

By ዮሐንስ ደርበው

February 09, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሌሊቱ 7:34 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው መነን አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በአደጋው አንዲት እናት ከስምንት ዓመት ልጇ ጋር ሕይወታቸው ሲያልፍ፥ የሟች የትዳር አጋርና የሕጻን ልጁ አባት በቃጠሎው ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በእሳት አደጋው አራት መኖሪያ ቤቶች የወደሙ ሲሆን÷ አደጋው ተስፋፍቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠር ሦስት የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ 24 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተሠማርተዋል፡፡

እሳቱን ለመቆጣጠርም 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ መፍጀቱ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!