Fana: At a Speed of Life!

አካዳሚው ከሩሲያ ጋር በስልጠናና በምርምር መስኮች የመስራት ፍላጎት አለው – ዶ/ር ምህረት ደበበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከሩሲያ ጋር በስልጠናና በምርምር መስኮች በመስራት የተቋሙን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ ገለጹ፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረኺን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ምህረት ደበበ እንደተናገሩት ፥ አካዳሚው እንደ አዲስ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋቋመ ጀምሮ የመንግስትንና የግል ተቋማትን አመራሮች በተሟላ የስልጠና ማዕከል ውስጥ እያሰለጠነ ነው፡፡

ይህንንም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተቋማዊ ሪፎርም እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ተቋማዊ ሪፎርሙ ሲጠናቀቅም አካዳሚው ሊያከናውናቸው ያቀዳቸው በርካታ ሀገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ፕሮግራሞች መኖራቸውን የጠቀሱት ምህረት ፥ ይህንንም ለማሳካት ተቋሙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ስትራቴጂያዊ አጋርነትን በመመስረትም የአካዳሚውን ተልዕኮ ለማሳካት እየተሰራ እንደሆነ የተናገሩት ርዕሰ አካዳሚው ፥ ከሩሲያ ጋር በስልጠና እና በምርምር መስኮች በመስራት የተቋሙን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸውም ነው የተናገሩት።

አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረኺን በበኩላቸው ፥ ከአካዳሚው ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን ከአካዳሚው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በቀጣይ በሚደረጉ ውይይቶችም የሚዳብር ሀሳብ እንዳላቸው አስታውሰው ፥ አካዳሚው ላደረገላቸው መልካም አቀባበልና ግብዣ አመስግነዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.