የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ቡድን 442 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

February 09, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ቡድን 442 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ።

የዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ቡድን ሊቀመንበር እንዳልካቸው ዘውዴ ÷ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፉን ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዶክተር ሊያ በበኩላቸው ÷ ቡድኑ ላደረገው ድጋፍ ያመሠገኑ ሲሆን ፣ በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የወደሙ የጤና መሰረተ ልማቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ለሚደረገውን ጥረት ዳያስፖራዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዓለም አቀፉ የዳያስፖራ የተግባር ቡድን በፈረንጆቹ መጋቢት 2022 እንደተቋቋመ መረጃዎች ያሳያሉ።

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!