የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ

By Alemayehu Geremew

February 10, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር በድጋሚ ዓለም አቀፍ ጨረታ አወጣ።

አሁን የወጣው ጨረታ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ለዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ለማቅረብ ያለመ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ኩባንያዎችም የማይመለስ 20 ሺህ ዶላር እና መተማመኛ በ13 ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደሚችሉም ነው የገለጸው።

የጨረታ ሰነዳቸውን telecombid@mofed.gov.et በመግባት ማቅረብ እንደሚችሉ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።