Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ ከኃይል ሽያጭ ከ12 ቢሊየን ብር በላይ አገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከኃይል ሽያጭ ከ12 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

126 ሺህ 101 አዲስ ኃይል ደንበኞችን ማፍራቱንም ነው አገልግሎቱ ያመለከተው።

እንዲሁም 51 የገጠር ከተሞች አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝተዋል ብሏል።

በ2014 በጀት ዓመት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የነበረውን የደንበኞች ቁጥር÷ እስከ ተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ማድረስ መቻሉም ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ሽፋንም 48 በመቶ መድረሱን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

የድኅረ ክፍያ ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሒሳብ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በቴሌ ብር፣ በሲ ቢ ኢ ብር 707070 ፣ በኢንተርኔት ባንኪግ እና በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በፖስ ማሽን እየከፈሉ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ደግሞ በተቋሙ ባሉ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት አገልግሎቱን እያገኙ ነው ተብሏል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.