የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ የተፈቀደ ሰልፍ እንደሌለ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል አስታወቀ

By Tamrat Bishaw

February 10, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዋሳ ከተማም ሆነ በክልሉ የትኛውም አካባቢዎች ላይ በመንግስት የተፈቀደ ሰልፍ እንደሌለ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል አስታውቋል፡፡

ግብረ-ሀይሉ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ በማካሄድ የተለያዩ የውሳኔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡ ተገልጿል፡፡

የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በመንግስት የተቀመጠውን አቅጣጫ በመተላለፍ የሚደረጉ ያልተፈቀደና ያልታወቀ እንቅስቃሴዎችን እንዲቆጣጠር ለፀጥታ አካሉ አመራር ተሰጥቷል።

ክልከላዎቹን የሚተላለፍ ማንኛውም አካል ለሚደርሰው ጉዳት በራሱ ሀላፊነት የሚወስድ እንደሆነ በውይይቱ መገለጹን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡