Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመቱ ከ1 ሺህ በላይ ደረጃዎች ጸደቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 1 ሺህ 435 ደረጃዎች መጽደቃቸውን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ከጸደቁት መካከል 268 ከዚህ በፊት ያልተዘጋጁ እና አሁን ተዘጋጅተው የቀረቡ “አዲስ” ደረጃዎች መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ይስማ ጅሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም 327 ደረጃዎች ከዚህ በፊት ተዘጋጅተው ሥራ ላይ ያሉ እና አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በቴክኒክ ኮሚቴው በስልታዊ ግምገማ ታይተው ማስተካከያ የተደረገባቸው ነባር “የተከለሱ” ደረጃዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም 840ዎቹ ደረጃዎች ደግሞ በስልታዊ ግምገማ ሲፈተሹ ምንም ለውጥ ሳይደረግባቸው ባሉበት ሁኔታ እንዲቀጥሉ የተባሉ “በማስቀጠል” መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡

ኢንስቲትዩቱ ደረጃዎችን የሚያዘጋጀው በምግብና ግብርና ውጤቶች፣ በጨርቃጨርቅና ቆዳ፣ በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች እንዲሁም በመሰረታዊና አጠቃላይ ደረጃዎች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም በኮንስትራክሽንና ሲቪል ምህንድስና፣ በኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሮመካኒካል እንዲሁም በአካባቢ እንክብካቤና ጤና ዘርፎች ኢንስቲትዩቱ ደረጃዎችን እንደሚያዘጋጅ ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.