Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ6ኛ ዙር የምረቃ ሥነ ስርዓት 132 የጤና ባለሙያዎችን አስመርቋል።

ከእነዚህ መካከል 22ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ ዶክትሬት የሠለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ በስምንት ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዑባህ አደም ከተመራቂዎቹ መካከል 52ቱ ሴቶች መሆናቸውን አመላክተዋል።

ኮሌጁ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ 561 የጤና ባለሙያዎችን ማስመረቅ መቻሉንም ጠቁመዋል።

11 አመት በዘለቀው የመማር ማስተማር ሂደቱም ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለማህበረሰቡ አበርክቷል ብለዋል።

በኢዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.