Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ11ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተካፈለች ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልዑክ በቦትስዋና ጋቦሮኒ እየተካሄደ በሚገኘው 11ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተካፈለ ነው።
በስብሰባው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና የልዩ የኢኮኖሚ ዞን ልማት ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም በ14ኛው ከፍተኛ የንግድ የስራ ሃላፊዎች የሚቀርበው ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዶበት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል::
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.