Fana: At a Speed of Life!

በሥድሥት ወሩ ለ8 ሺህ 801 አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ሥድሥት ወር ለ8 ሺህ 801 አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ መስጠቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) አስታወቀ፡፡

የጥራት ማረጋገጫ የተሰጠው በባዮ ኬሚካል ፍተሻ ዘርፍ (በኬሚካልና ማዕድን ፍተሻ ቤተሙከራ፣ በምግብና መጠጥ ቤተሙከራ፣ በግብርና ምርቶችና ግብዓቶች ፍተሻ ቤተሙከራ፣ በማይክሮባዮሎጂ ፍተሻ ቤተ ሙከራ እና በጨረራ ፍተሻ ቤተሙከራ) ነው፡፡

እንዲሁም በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ ደግሞ (በሜካኒካል፣ በኤሌክትሪካል፣ በጨርቃ ጨርቅና ስቴሽነሪ፣ በቆዳና የፓኬጂንግ ማቴሪያል) ላይ የጥራትና ቁጥጥር ማረጋገጫ መስጠቱንም ያስታወቀው።

በተጨማሪም የኢትዮጵያን እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን መሰረት በማድረግ ለ702 ሺህ 455 ነጥብ 55 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ምርት እና የአፈር ማዳበሪያ ላይ የጥራት ማረጋገጫ መሰጠቱን አስታውቋል።

እንዲሁም በ20 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት ላይ የጥራት ማረጋገጫ መሰጠቱን የድርጅቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ተኪኤ ብርሃነ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል 500 የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት መሰጠቱንም ነው የገለጹት፡፡

አምራቾች ለጥራት ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ የምርቶቻቸውን እና የአገልግሎታቸውን ጥራት በ3ኛ ወገን ጥራቱን ማረጋገጥ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በመረዳት የምርታቸውን ጥራት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።

በዮሐንስ ደርበው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.