ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአሜሪካ ጦር በካናዳ አየር ክልል ምንነቱ ያልታወቀ በራሪ ቁስ መትቶ መጣሉን ገለጸ

By Melaku Gedif

February 12, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ በራሪ ቁስ በሰሜን ምዕራብ ካናዳ አየር ክልል ውስጥ መትቶ መጣሉ ተሰምቷል፡፡

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስቴር ጀስቲን ትሩዶ ÷ ምንነቱ ያልታወቀው ቁስ አካል በአሜሪካ ኤፍ-22 በተሰኘ ተዋጊ ጄት ተመትቶ መውደቁን ተናግረዋል፡፡

ምንነቱ ያልታወቀው ቁስ በካናዳ አየር ክልል እንዲመታ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ስለጉዳዩ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር መነጋገራቸውን አንስተዋል።

የካናዳ ወታደራዊ ሃይሎች የቁሱን ምንነት ለማወቅ ምርመራ ማድረግ መጀመራቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ያስታወቁት፡፡

የካናዳ የመከላከያ ሚኒስትር አኒታ አናንድ በበኩላቸው÷ ምንነቱ ያልታወቀው በራሪ ቁስ አካል በ40 ሺህ ጫማ ወይም በ122 ሺህ ሜትር ርቀት ሲበር እንደነበር መጠቆማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡