Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያ መስመርን ሳታፈነዳ አልቀረም ተባለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከሞስኮ ወደ በርሊን የተዘረጋውን “ኖርድ ስትሪም” የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ሳታፈነዳ አልቀረም ተባለ፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እንደሚሉት አሜሪካ የሩሲያን እና የጀርመንን ትብብር እንደ ሥጋት ትመለከተዋለች፡፡

ላለፉት 20 እና 30 ዓመታት ሀገራቱ ጠንካራ ግንኙነት እንደነበራቸውም ላቭሮቭ ማስታወሳቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ሩሲያ ለጀርመን በምታቀርበው የኃይል አማራጭ እና ጀርመን በአጸፋው ለሩሲያ በምትልከው ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ደግሞ በኮርፖሬሽኖቿ የዓለምን ገበያ በብቸኝነት መምራት ለምትሻው አሜሪካ የሚዋጥ አልሆነም ሲሉም ነው ላቭሮቭ የገለጹት ፡፡

በመሆኑም አሜሪካ ከሞስኮ በበርሊን አድርጎ ለአውሮፓ ሀገራት ጋዝ ለማድረስ የሚያገለግሉትን “ኖርድ ስትሪም” 1 እና 2 የጋዝ ማስተላለፊያ መሥመሮች መትታለች ብለዋል፡፡

ለዚህም በዋቢነት በፖለቲካ ጉዳዮች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ቪክቶሪያ ኑላንድ ÷ ሴኔታቸው ፊት የተናገሩትን አንስተዋል።

ኑላንድ ÷ “ኖርድ ስትሪም 2” የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር አሁን ላይ በባሕር ውስጥ ያለ ስብርባሪ ብረት መሆኑን በማወቄ እርካታ ይሰማኛል ነው ያሉት።

አያይዘውም የአሜሪካ አስተዳደርም ሐሳቤን ይጋራል ብዬ እገምታለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.