Fana: At a Speed of Life!

የአቅም ማሻሻያ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

  1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።
  2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.