ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቻይናዋ ውሃን ከተማ ከ11 ሳምንታት በኋላ ተከፍታለች

By Tibebu Kebede

April 08, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባት የቻይናዋ ውሃን ከተማ ከ11 ሳምንታት በኋላ ተከፍታለች።

ቫይረሱ ከተገኘ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 11 ሳምንታት ተዘግታ የቆየችው ከተማ ዳግም ተከፍታ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ገብታለች።

ከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ተዘግታ ቆይታ ነበር።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በመንግስት የተላለፈውን ትዕዛዝ ተቀብለው ቤታቸው ውስጥ አሳልፈዋል።

አሁን ላይ በተወሰዱ እርምጃዎች የስርጭት መጠኑን መቆጣጠር በመቻሉ ከተማዋ ዳግም ተከፍታለች።

እንደ ባቡር ያሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎችም ስራ ጀምረዋል ነው የተባለው።

በምርመራ በቫይረሱ አለመያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎችም በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸዋል ተብሏል።

ነዋሪዎች መደበኛ እንቅስቃሴ መከፈቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየትም ዓለም ከእኛ ይማራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

በውሃን ከተማ 11 ሚሊየን ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን፥ በቻይና በቫይረሱ ለህልፈት ከተዳረጉት መካከል ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበበት መሆኑ ይነገራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ