Fana: At a Speed of Life!

6 አዳዲስ ምርቶችን ወደ ወጪ ምርት በማስገባት ከ7 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት አዳዲስ ምርቶችን ወደ ወጪ ምርት (ኤክስፖርት) ለማስገባት ታቅዶ ሥድስት አዳዲስ ምርቶችን በማስገባት 7 ነጥብ 58 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት 915 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያላቸው ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርት እንዲተኩ መደረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሀገር ውስጥ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ ለመተካት በተከናወነው ሥራ 41 ነጥብ 28 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ሚኒስቴሩ ባቀረበው የሥድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ተገልጿል፡፡
ከተሰጠው የምርት ትዕዛዝም 90 ነጥብ 78 በመቶ መመረቱ ነው የተመለከተው፡፡

በግማሽ ዓመቱ ተጨማሪ 35 ከፍተኛ ደረጃ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ 47 ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል ለአምራች ኢንዱስትሪ 303 ሚሊየን ዶላር ለማቅረብ ቢታቀድም ማቅረብ የተቻለው 128 ሚሊየን ዶላር ብቻ መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ምርምርና ስርፀትን በተመለከተ 16 ምርምሮች ወደ ተግባር ተቀይረዋል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያ ታምርትን በዘላቂነት በመደገፍ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ማነቆዎችን ለመፍታት ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ የሚያስችል የተጠያቂነት አሠራር መዘርጋት እንዲሁም የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ጫና መጠበቅ በትኩረት የሚሠራባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.