Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የተመዘገቡ የምግብ ምርቶች ብዛት 11 ሺህ 301 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስካሁን የተመዘገቡ የምግብ ምርቶች ብዛት 11 ሺህ 301 መድረሳቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት የመዘገበው የምግብ ምርቶች ብዛት 1 ሺህ 419 መሆኑን ገልጾ÷ እስካሁን የመዘገባቸው የምግብ ምርቶች ብዛትም 11 ሺህ 301 መድረሳቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ 38 የምግብ ዓይነቶች ላይ 717 ናሙና ተወስዶ በተደረገው የጥራት ምርመራ 60 ናሙናዎች የኢትዮጵያን ደረጃ ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጓል ብሏል፡፡

በተለያየ ምክንያት ለሰው ልጆች ምግብነት የማይውልበት ደረጃ ላይ የደረሰ 382 ቶን የሚጠጋ የምግብ ምርት መወገዱንም ነው ባለስልጣኑ የገለጸው፡፡

እንዲሁም ከ1 ሚሊየን 148 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው መድኃኒቶችና የመድኃኒት ግብዓቶች በተለያየ ምክንያት ለሰው ልጅ አገልግሎት እንዳይውሉ ተደርጓል ተብሏል።

ከ13 ሚሊየን 336 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው አስገዳጅ መስፈርት ያላሟሉ እና ከባለስልጣኑ ፈቃድ የሌላቸው የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እንዳይሰራጩ አድርጌአለሁ ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

በሌላ በኩል ከ84 ሚሊየን 832 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የውበት መጠበቂያ እና የውበት መጠበቂያ ጥሬ ዕቃዎች÷ ገላጭ ጽሑፍ ስለሌላቸው እና ከተቋሙ ፈቃድ ውጭ በመመረታቸው እንዳይሰራጩ መደረጉን ነው ባለስልጣኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስታወቀው፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.