ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ በቱርክና ሶሪያ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስካሁን ከ35 ሺህ የሚበልጡ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ኢትዮጵያ እና ቱርክ በተለያዩ ዘርፎች የቆየና ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ አንስተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ የተሰማቸውን ሀዘን በቱርክ ኤምባሲ በተከፈተው የሃዘን መዝገብ ላይ ማስፈራቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡