በመተከል ዞን የእርቀ ሰላም ስምምነት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በአራት ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር የእርቀ ሰላም ስምምነት ተካሄደ፡፡
በመከላከያ ሰራዊት የሜካናይዝድ ክፍሉ ስነልቦና ግንባታ ኃላፊ ሻለቃ መስፍን አስራት÷ መንግስት የሰጠው የሰላም አማራጭ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተደረገው የሰላም ስምምነት ለሀገር እድገትና አንድነት ትልቅ ዋጋ አለው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዳንጉር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ፓርሻዊ ኡስማን እንደገለጹት÷ በፀጥታ ኃይሉ የተገኘውን ዘላቂ ሰላም በማስጠበቅ ለዘላቂ ልማት የሚደራጅ አምራች ኃይል እየፈጠሩ መቀጠል ይገባል፡፡