Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተመራ የልዑካን ቡድን በኦሮሚያ እና ደበብ ክልሎች እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በምስራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ እና በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ከመንግስትና ከሲ አይ ኤፍ በተደረገ ድጋፍ እየተሰሩ የሚገኙ የዋተር ፎር ላይፍ ፕሮጀክቶችን ነው የጎበኘው፡፡

በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውሃን እንዲሁም አማራጭ የሶላር መብራቶችን ለማዳረስ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የተጀመሩ የመብራትና የውሃ ፕሮጀክቶችም በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት መጠናቀቅ እንደሚገባቸው ልዑካን ቡድኑ በግምገማው ወቅት አሳስቧል፡፡

ፕሮጀክቱ በመንግስትና ሲ አይ ኤፍ በተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት በተመደበ በጀት1 ሺህ 52 የጤና ተቋማትና 1 ሺህ 52 ትምህርት ቤቶች ውሃና መብራት የሚያገኙበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ፕሮጀክቱ በተመሳሳይ በ8 ክልሎች እና በ10 ወረዳዎች እየተሰራ እንደሚገኝ በመርሐ ግብሩ መገለፁን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.