Fana: At a Speed of Life!

ከርዕደ-መሬት አደጋው 9 ቀናት በኋላ በሕይወት የተረፉ የ77 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ተገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቱርክ እና ሶሪያ ከደረሰው የርዕደ-መሬት አደጋ ዘጠኝ ቀናት በኋላ አንዲት የ77 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ ሴት በሕይወት መገኘታቸው ተገለጸ፡፡

ግለሰቧ አዲያማን በተባለች በደቡብ ምሥራቅ ቱርክ በምትገኝ አካባቢ ፍርስራሽ ውስጥ ነው በሕይወት ተገኙት፡፡

ዛሬ የወጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት በሀገራቱ በተከሰተው ርዕደ-መሬት እስከ አሁን ከ 41 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በቱርክ 35 ሺህ 418 እንዲሁም በሶሪያ ከ 5 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

የተመድን የሰብዓዊ አቅርቦት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከቱርክ በባብ – አል – ሳላም ወደ ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ እየሄዱ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ተመድ በሕይወት ለተረፉ አምሥት ሚሊየን ሶሪያውያን መጠለያ፣ የጤና መጠበቂያ እና ምግብ ለማድረስ 397 ሚሊየን ዶላር እንደሚስፈልገው ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.