Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለሶሪያ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሀገራት በርዕደ መሬት ጉዳት ለደረሰባት ሶሪያ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ፀሀፊው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት÷ ዕርዳታው ከሁሉም ወገን መሰብሰብ እንዳለበት እና ገንዘቡ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ፍላጎትን ይሸፍናል ብለዋል።

ተመሳሳይ ድጋፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ሰዎች እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል።

ርዕደ መሬቱ ከተከሰተ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ የ50 ሚሊየን ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ቢሰጥም በቂ እንዳልሆነ መግለጻቸውን ከጽ/ቤቱ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የድጋፍ ጥሪው መላውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሰራር ስርዓት እና የሰብአዊ አጋሮችን አንድ ላይ በማሰባሰብ ወደ 5 ሚሊየን የሚጠጉ ሶሪያውያንን በመጠለያ ፣ በጤና አጠባበቅ ፣ በምግብ እና እንክብካቤ ህይወት አድን እርዳታ ለማግኘት ያስችላል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.