ኢትዮጵያ እና ኬንያ የተፈራረሟቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም ገመገሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ ቀደም ሲል የተፈራረሟቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም ገምግመዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና ፀሐፊ ኮሪር ሲንግ ኦይ ጋር በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱ የተካሔደው ከአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን መሆኑን የውጭ ጉይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ በንግዱ ዘርፍ እንዲሁም በሰዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ እና ከሀገራቱ አገልግሎቶችን የማግኘት መብት ላይ ቀደም ሲል የተፈራረሟቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም ገምግመዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!