Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ ዓለምአቀፍ ትብብር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ ዓለምአቀፍ ትብብር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሺር ኦማር ጃማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በቀጣይም በፀጥታና ደኅንነት፣ በመሠረተ ልማት እና በኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ላይ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን÷ በሞቃዲሾ የተካሄደው የአጎራባች ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የጉባዔውን ውሳኔዎች ተግባራዊ እንደምታደርግም ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አብሺር ኦማር ጃማ በበኩላቸው÷ በሞቃዲሾው የአጎራባች ሀገራት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ እያበረከተች ያለውን ሚና አድንቀዋል።

ሶማሊያ የፕሪቶሪያውን የሠላም ስምምነት እንደምትደግፍ እና ዝርዝር አፈፃፀሙን ለማቀላጠፍ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምታደንቅ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት መተባበር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.