Fana: At a Speed of Life!

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ አሁንም ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ አሁንም ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ ለዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ የተሰጠው ዓለም አቀፋዊ ምላሽ መሻሻል እንደታየበት አንስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ በጥቂት ሀገራት ቀጣይነት ያለው በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን ÷ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ድርጅቱ የዝንጀሮ ፈንጣጣ አሁንም የዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን አረጋግጫለሁ ማለቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የቅርብ ጊዜ አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ፥ በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የወረርሽኙ ስጋት መካከለኛ እንደሆነ ተገምግሟል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የተቀናጀ የህብረተሰብ ጤና እርምጃዎችን ለመምራት በጥር 2022 የተጀመረውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ለመከላከል ያለው ዝግጅትና ምላሽ እቅድ በሰኔ 2023 ይጠናቀቃል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.