የሀገር ውስጥ ዜና

ጎንደር ዩኒቨርሲቲና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By Amele Demsew

February 16, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እና የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ ተፈራርመውታል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እንደገለፁት÷ በጋራ መስራቱ የትምህርት ጥራትን እና የጤና አገልግሎት ተግባራትን በስኬት ለማከናወን ያግዛል፡፡

ዶክተር መሳይ ሃይሉ በበኩላቸው ÷የህብረተሰብ ጤና ችግሮችን በመከላከልና በመቆጣጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የጎንደር ቀጠና ሰፊ የጎረቤት ሀገራት ድንበር ተጋሪ በመሆኑ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር በጋራ መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በተለይም ከዩንቨርሲቲው ጋር በተለይም ትኩረት በሚሰጣቸው የህብረተሰብ ጤና ችግሮች ላይ የበለጠ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከልና ተላላፊ በሽታዎችን በመቆጣጠር ረገድ በጋራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

በሙሉጌታ ደሴ