Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 185 የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ስራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 185 አዳዲስ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ስራ አስጀመረ።

የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ስራ ባስጀመሩበት ወቅት÷በሀገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የገቢ እና ወጪ ንግድ አገልግሎቱን ለማፋጠን ድርጅቱ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

ለአብነትም የከባድ የየብስ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለማስፋት በተደረገው ጥረት ከ2013 ዓ.ም ወዲህ  373 ከባድ ተሽከርካሪዎች ግዥ ተፈፅሞ ወደ ስራ መግባታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ዛሬ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 185 አዳዲስ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችም ስራ እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ የድሬድዋ ወደብ ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሱት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ ዴጌ ቦሩ በበኩላቸው÷አዳዲስ ተሽከርካሪዎች የወጪ ገቢ ንግድን ከማሳለጥ አኳያ የማይተካ ሚና እንዳላቸውም ጠቅሰዋል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ 572 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተጠናከረ የጭነት አገልግልሎት እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.