የሀገር ውስጥ ዜና

የፓኪስታን ባለሐብቶች በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ እንዲሰማሩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ቀረበላቸው

By Alemayehu Geremew

February 17, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን ባለሐብቶች በጤናው ዘርፍ መዋዕለ-ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ የኢንቨስትመንት አማራጭ ቀረበላቸው፡፡

ኢትዮጵያ አማራጮቹን ይፋ ያደረገችው በፓኪስታን በተካሄደው የፋርማሲ ቁሶች እና የጤና መጠበቂያ ምርቶች ኤክስፖ ላይ ነው፡፡

በኤክስፖው በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንዔል ተሬሳ በፓኪስታን ላሆር ከተማ በተካሄደው “የፋርማ ኤክስፖ” የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በፋርማሲው ዘርፍ እና በጤና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ከተሠማሩ ባለሐብቶች ጋርም ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ልዑካኑ ከሀገሪቷ ፌዴራላዊ እና ክልላዊ ንግድ ምክር ቤቶች ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሮች እንዲሁም ከሀገሪቷ የኢንቨስትመንት ማስታወቂያ ኤጀንሲ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ጋር መምከራቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡