የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ

By Feven Bishaw

February 17, 2023

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በ36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የሌሴቶ ፕሬዚዳንት ሳም ማትኬኔ፣ የኬፕ ቬርዴ ፕሬዚዳንት ሆዜ ማሪያ ፔሬራ፣ የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ንዩሲ፣ የሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋውዛኒ እና የቻድ ፕሬዚዳንት መሃማት ኢድሪስ ዲቤ  አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚደንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 11 እና 12 “የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ ይካሄዳል።