የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከተመድ ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአፍሪካ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሊቀመንበሩ በአፍሪካ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ ድሎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ኋላ የመመለስ ስጋት እንዳይኖርባቸው በጋራ ሊሠሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል።
የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ የካቲት ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።