Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል 182 ሺ ሰዎች የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል- የክልሉ ጤና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል 182 ሺ ሰዎችን የጤና መድህን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ ገለፁ።

በክልሉ የ2015 የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ንቅናቄ ማጠቃለያ እና የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

በዚህ ዓመት በጥር ወር ውስጥ በተደረገ የአንድ ወር የንቅናቄ ዘመቻ ብቻ 170 አዳዲስ አባወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አቶ ያሲን ተናግረዋል።

በመርሐ-ግብሩ የሀረሪ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦርዲን በድሪ ጤናማ የሆነ ማህበረሰብ ለማፍራት ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ አየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አቶ ኦርዲን አክለውም፦ ህብረተሰቡን የጤና መድህን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በአመለካከት፣ በእውቀት እና በክህሎት ብቁ የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ደረጃም ክልሉ ከዚህ የበለጠ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

በመቅደስ ደረጀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.