በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሚታዩ አስቸኳይ ጉዳዮች ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ክስ አንዱ እንዲሆን መመሪያ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሚታዩ ጥቂት አስቸኳይ ጉዳዮች ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ክስ አንዱ እንዲሆን መመሪያ መሰጠቱን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ገለፁ።
ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል ህብረተሰቡ በቤት በሚቆይበት ወቅት በቤት ውስጥ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ሊጨምሩ እንደሚችሉ በማሰብ መመሪያው የወጣው።
በመመሪያው መሰረትም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜያት ከሚያዩቸው ጥቂት አስቸኳይ ጉዳዮች ውስጥ የቤት ውስጥ ጥቃት ክስ እንዲሆን መመሪያ መሰጠቱን ነው የገለፁት።
የኮሮና ስርጭትን ለመከላከል ህብረተሰቡ በቤት እንዲቆይ በሚደረግበት ወቅት በቤት ውስጥ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ሊጨምሩ እንደሚችሉ ታስቦ የፌደራል ፍ/ቤቶች ከሚያዩቸው ጥቂት አስቸኳይ ጉዳዮች መሐል የቤት ውስጥ ጥቃት ክስ እንዲሆን መመሪያ ተሰጥቷል።
— Meaza Ashenafi (@ashenafi_meaza) April 9, 2020
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision