በኢትዮጵያን በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የሚቀርበው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ተመድ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያን በጦርነቱ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚቀርበው ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ቴት ገለጹ።
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ዋና ጸኃፊ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴት ÷የአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ተስፋና እድል ያለው ክልል ነው ብለዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት በቀጣናው መረጋጋት ለማስፈንና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የጸጥታ ችግር መንስዔዎችን መከላከል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የድርጅቱ ትኩረትም በቀጣናው ያሉ አባል ሀገራት በልማት ሥራዎችና በምጣኔ ኃብት ግቦች ላይ እንዲያተኩሩ መርዳት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የሰብዓዊ ድጋፍ በጦርነቱ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች እየቀረበ መሆኑን ገልጸው÷ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በቀጣይም መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት ሥራዎች ለመደገፍ የገንዘብና የግብዓት ድጋፍ ለመሰብሰብ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ሰላም እንዲጠናከርና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማጠናከር እንደሚሰራ አመላክተዋል።
በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው የሰላም ሂደት የሚደነቅና ተስፋ ሰጭ መሆኑን አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ በገር ውስጥና ከአገር ውጪ የምጣኔ ኃብታዊ ትስስርን ለማጎልበት እየሰራች ያለውን ሥራ የሚበረታታና መቀጠል ያለበት ነው ማለታቸውንም ኢዘኤ ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!