የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከፋኦ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Tamrat Bishaw

February 17, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኪዩ ዶንግዩን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም ድርጅቱ ኢትዮጵያ የምግብና የሥነ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ አደጋን የመቋቋም አቅሟን ለመገንባት የግብርና ልማትን በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ አጋር በመሆን ላደረገው አስተዋጽዖና ድጋፍ ማመስገናቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።