Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችንና ረቂቅ አዋጆችን አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ በሁለተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ ሹመቶችን እና ሁለት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ።

ጨፌው በተሻሻሉት የኦሮሚያ የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር እና የኢንቨስትመንት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ አዋጅ ቁጥር 249/2015 መሰረት በማድረግ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ የገጠር መሬት በሕግ አግባብ እንዲመራ በማድረግ አርሶ አደሩ፣ አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮችን የመሬት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አርሶ አደሩ በዘመናዊ መልኩ ያለውን መሬት በማስመዝገብ መሬትን በማስያዝ ብድር እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሕገ ወጥ መልኩ የሚያዝን መሬት ለመቆጣጠርና ህገ ወጥነትን ለመከላከል ያግዛል ተብሏል።

በጨፌው የተለያዩ ሹመቶች የተሰጡ ሲሆን÷ በዚሁ መሰረት

1. ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፀጥታ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ

2. አቶ መስፍን መላኩ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ

3. አቶ ሁሴን ፈይሶ – የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

4.ወ/ሮ ኮኮቤ ዲዳ – የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ

5. አቶ አህመድ ኢድሪስ – የኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

6. ጉዮ ዋሪዮ- የጠቅላይ ዐቃቤ ቢሮ ኃላፊ

7.አቶ ጌቱ ገመቹ – የግብርና ቢሮ ኃላፊ

8.አቶ መሀመድ ጉዬ – የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ዳንኤል ቸርነት – የንግድ ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ ማቲዎስ ሰቦቃ – የስራ እድል ፈጠራ እና ሙያ ቢሮ ኃላፊ

11. ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ – የመስኖና የአርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ

12. ዶ/ር አደሬ አሰፋ – የልማት ድርጅቶች ቢሮ ኃላፊ

እንዲሁም አቶ በድሪ ተማም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ተሹመዋል፡፡

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.