ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ዳይሬክተር ሜሪ ካትሪን ፒ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ላይ መምከራቸውም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት መሀመድ አል ጃስር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ላሉ አዳዲስ እንቅስቃሴዎች የተለያየ ድጋፍ ማፈላለግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!