Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ያሠለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና የአርዳይታ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ያሰለጠኗቸውን 786 ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ10 የተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸው 202 ተማሪዎች አስመርቋል።

እንዲሁም የአርዳይታ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን 584 ተማሪዎች በደረጃ አራት አስመርቋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷  ሚኒስቴሩ በስሩ በሚገኙ የግብርና ኮሌጆች ተማሪዎችን እያሰለጠነ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመንና በማሻሻል የበርካታ ስራ እድሎች መፈጠሪያ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ተመራቂዎችም የኢትዮጵያ አርሶ አደር ካለበት ችግር ለማውጣትና ለማዘመን ሚናቸው ብዙ መሆኑን  አመላክተዋል።

በኦሊያድ በዳኔ እና በታምሩ ከፈለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.