የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

February 18, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር መወያየታቸውን ገለጹ፡፡

በዚህም ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ ከፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ፣ ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና ከፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳዪሺሚዬ ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ከሀገራቱ መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይትም በቀጣናዊ እና በጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው ያመላከቱት፡፡