ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ የላከችው የቁሳቁስ ድጋፍ እና የነፍስ አድን ቡድን ጋዛንቴፕ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቱርክ በተከሰተው ርዕደ መሬት ምክንያት ትናንት ወደ ቱርክ የላከችው የቁሳቁስ እና የነፍስ አድን ቡድን አደጋው በደረሰበት ጋዛንቴፕ መድረሱ ተገለጸ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ በተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ገልጸው÷ ኢትዮጵያ የተቸገረ ወዳጅዋን ለመርዳት ምንጊዜም ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀው ነበር፡፡
በዚሁ መሰረት ትናንት አመሻሽ ላይ ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ የላከችው የቁሳቁስ ድጋፍ እና የነፍስ አድን ቡድን አደጋው በደረሰበት ጋዛንቴፕ መድረሱን በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም ሞሐመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡