Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች አቀባበል አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች በቤተ መንግስት አቀባባል አደረጉ ።
አቀባበል የተደረገላቸው የ12 የአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች እና ልዑካቸው በ27ኛው መደበኛ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ተቋም አጠቃላይ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተሳተፉ ያሉ ናቸው፡፡
በአቀባበል ሥነ ስርዓቱ ላይ የተለያዩ ባህላዊ የኢትዮጵያ ምርቶች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ሀገር በቀል ምርቶቹን ከማስተዋወቅ አንጻርም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።
ጉባዔው ከየካቲት 8 ቀን 2015 ጀምሮ በስርዓተ ጾታ እኩልነት የሚታየውን ክፍተት መዝጋት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡
በፍሬሕይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.