የሀገር ውስጥ ዜና

ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የማደርገው ድጋፍ ይቀጥላል – ተመድ

By Alemayehu Geremew

February 18, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው በውይይታቸው ላይ እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያን የሰላም ሂደት አድንቀዋል።

ድጅቱ ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

የድርጅቱ መሥራች አባል ከሆነችው ኢትዮጵያ ጋር ያለውን የቆየ የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንሠራለን ብለዋ ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡