Fana: At a Speed of Life!

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት እንቅስቃሴዎቹ ሳይንሳዊ ዘዴን መከተል አለባቸው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንቅስቃሴዎቹ ሳይንሳዊ ዘዴን መከተል እንዳለባቸው ምሁራን አመላከቱ፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት ከዘርፉ ወሳኝ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩ በቤት ልማት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በከተማ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ያለመ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ረሻድ ከማል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ መድረኩ በመንግስት ተቋማት ትልቅ ችግር ሆኖ የሚነሳውን በሥራ ሒደት፣ የተገኙ ተሞክሮዎችን የማስፋትና የተቋም ታሪክ መዝግቦ ለተተኪ አመራርና ሠራተኞች የማስተላለፍ ክፍተት ለመሙላት ይጠቅማል፡፡

የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት እንቅስቃሴዎቹ ሳይንሳዊ ዘዴን መከተል እንደሚገባቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸራልና ሕንጻ ኮንስትራክሽን ኢኒስቲትዩት መምህር ዶክተር ዘገየ ቸርነት እና የኦቪድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ በመድኩ ላይ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፎች አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.