Fana: At a Speed of Life!

የቻይና አፍሪካ ወዳጅነትን ለማጠናከር ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ዢ ሺን ፒንግ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና አፍሪካ ወዳጅነትን ለማጠናከር ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ሺን ፒንግ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ለ36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ መልዕክት ሲያስላልፉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዢ ፥ ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ህብረት በዓለም ላይ የተፈጠሩ ችግሮች በንቃት እንዲፈቱ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ግንባታን በማፋጠን እና በማስታረቅ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን ጠቁመዋል።
አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያሳደረች ያለችው ተጽዕኖ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ፥ ለአፍሪካ ሀገራት እና ህዝቦች የላቀ ስኬትን ከልብ እመኛለሁ ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ፥ በ2022 የቻይና አፍሪካ ትብብር ሁለንተናዊ፣ ባለ ብዙ ደረጃ፣ ጥራት ባለው መልኩ እየጎለበተ የመጣና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር በተያያዘ የቻይና እና አፍሪካ ግንኙነት ግንባር ቀደም በመሆን ጥሩ የእድገት ግስጋሴ እንደነበረውም ነው ያነሱት።
የቻይና አፍሪካን ወዳጅነትና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር፣ በዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመቀናጀትና ለመተባበር እንዲሁም የወደፊት የጋራ ተጠቃሚነት ያለው የቻይና አፍሪካ ማህበረሰብ ግንባታን ለማስተዋወቅ ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.